301-565-4910     info@adulistax.com
What to Bring
What to bring at the time of your tax preparation:

Proof of identification (Drivers License, Government issued Photo I.D.)

Social Security Cards for you, your spouse and dependents and/or a Social Security Number verification letter issued by the Social Security Administration. If you or your dependent is not eligible to get a Social Security Number, you may need to obtain an Individual Taxpayer Identification Number (ITIN). We can help you do this.

Birth dates for you, your spouse and any dependents on the tax return.

Wage and earning statement(s) Form W-2, W-2G, 1099-MISC and 1099-R, from all employers and payers. If you have not received your Forms W-2 from your employer and want to know what to do, we can help. Call us.

Interest and dividend statements – Forms 1099-INT and 1099-DIV.

Social Security, State Income Tax refund and Unemployment Compensation statements – Forms SSA-1099 and 1099-G.

Information on Broker and Barter Exchange Transactions – Form 1099-B.

Records of rental income and expenses, IRA contributions, and alimony paid or received.

Mortgage Interest Statement – Form 1098; and records of the purchase or sale of your residence.

Records of medical, eye care and dental expenses.

Receipts for cash and non-cash charitable contributions such as your church or other religious organizations, government organization like federal or state police, public schools, or other charitable organization like, cancer centers and the likes.

A copy of last year’s Federal and State returns, if available.

Total amount paid for a day care provider and the day care provider’s tax identifying number – the provider’s Social Security Number or Employer Identification Number (EIN number).

To file taxes electronically on a married filing joint tax return, both spouses must be present to sign the required forms.

የገቢ ግብር ማስታወቂያዎን ለማሰራት ወደ እኛ ሲመጡ ምን ማምጣት አለቦት?

እርሶነቶን የሚያረጋግጥ መታወቂያ (የመንጃ ፈቀድ ወይም በመንግስት የተሰጥዎትን ፎቶ ያለበት መታወቂያ)

የእርሶን፣ የባለቤቶን እና የጥገኞቾን የሶሻል ሴኩሪቲ ካርድ እና/ወይንም የሶሻል ሴኩሪቲ ቁጥሮን የሚያረጋግጥ ከሶሻል ሴኩሪቲ አድምንስትሬሽን የተሰጥዎትን ደብዳቤ። እርሶ ወይንም ጥገኞቾ ሶሻል ሴኩሪቲ ቁጥር ማዉጣት ካልቻሉ የግለሰብ ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማዉጣት ይኖርቦታል። ይህንንም ማዉጣት እንዲችሉ ልንረዳዎ እንችላለን።

የእርሶን፣ የባለቤቶን እና የጥገኞቾን የትዉልድ ቀን።

የደምወዝ እና ገቢ መረጋገጫ ቅፅ W-2, W-2G, 1099-MISC እና 1099-R ከቀጣሪዎቾ እና ከፋዮቾ በሙሉ ተቀብለዉ ማምጣት አለቦ። W-2 ቅፅ ከቀጣሪዎቾ ካልተቀበሉ እና ምን ማደረግ እንደሚገባዎ ለማወቅ ከፈለጉ ይደዉሉልን በደስታ እንረዳዎታለን።

የወለድ እና የአክሲዮን ትርፍ ድርሻ ማስታወቂያ ቅጽ 1099-INT እና1099-DIV.

የሶሻል ሴኩሪቲ፣ የስቴት ገቢ ግብር ክፍያ ተመላሽ እንዲሁም የስራ አጥነት ካሳ ማስታወቂያ ቅፅ SSA-1099 እና 1099-G.

ስለ አገናኝ (ድለላ) እና አይነት ባይነት ልዉዉጥ ንግድ እንቅስቃሴ መረጃ ቅፅ Form 1099-B.

ስለ ኪራይ ገቢ እና ተዛማች ወጪዎች፣ አይአርኤ መዋጮ እንዲሁም የፍቺ ካሳ (አለሞኒ) ክፍያ ወይም ገቢ ማስረጃዎች።
የሞርጌጅ ወለድ ማስታወቂያ ቅፅ 1098 እንዲሁም የመኖሪያ ቤት ግዢ ወይንም ሽያጭ ሰነድ- ማስረጃ።

የህክምና፣ የአይን እንክብካቤ አገልግሎት እና የጥርስ ህክምና ወጪ ማስረጃዎች።

ለቤተ-ክርስቲያኖ ወይንም ለሌሎች የእምነት ተቌሞች ወይንም እንደ ፌደራል አና ስቴት ፖሊስ የመሳሰሉ የመንግስት ተቌማት፣ የህዝብ ትምህርት ቤቶች፣ ወይንም እንደ ካንሰር ሴንተሮች እና የመሳሰሉ ሌሎች በጎ አድራጎት ድርጅቶች በጥሬ ገንዘብ ወይንም ከጥሬ ገንዘብ ዉጪ ላዋጡት የበጎ አድራጎት መዋጮ የተሰጦትን የገቢ ደረሰኝ።

ያለፈዉ አመት የፌደራል እና ስቴት ግብር ማስታወቂያ ኮፕ፤ ማቅረብ ከቻሉ።

ለልጆቾ እንክብካቤ ለህፃናት መዋያ ተቌመት የከፈሉትን ጠቅላላ ክፍያ መጠን እና የህጻናት እንክብካቤ አቅራቢዉን ግብር መለያ ቁጥር፣ ሶሻል ሴኩሪቲ ቁጥር ወይንም የአሰሪ መለያ ቁጥር (በተለምዶ EIN በመባል የሚታወቀዉን ቁጥር)።

ጥንዶች የግብር ማስታወቂያቸዉን በጋራ የሚያሰሩ ከሆነ አስፈላጊዉን ቅፅ ለመፈረም ሁለቱም ግለሰቦች በቦታዉ መገኘት ይኖርባቸዋል።