301-565-4910     info@adulistax.com
Business Income Tax Tips
Business Income Tax Tips

The maximum depreciation limits for passenger automobiles; trucks and vans; and Sport Utility Vehicles (SUVs) and pickup trucks first placed in service during the 2014 calendar year are:

Passenger automobiles

  • $3,160 for the first tax year;
  • $5,100 for the second tax year;
  • $3,050 for the third tax year; and
  • $1,875 for each succeeding tax year.

Trucks and vans

  • $3,460 for the first tax year;
  • $5,500 for the second tax year;
  • $3,350 for the third tax year; and
  • $1,975 for each succeeding tax year.

Sport Utility Vehicles (SUVs) and pickup trucks it is $25,000.00.

For year 2014, the standard mileage rates for the use of a car is 56 cents per mile for business miles driven and 23.5 cents per mile driven for medical or moving purposes. In addition, the business standard mileage rate cannot be used for more than five vehicles used simultaneously.The rates can be used to figure the cost of the driving rather than keeping track of your actual car expenses. However, you still need to keep a record of your mileage, including notations on the date, odometer reading, destination, and purpose of each trip.

Business tax tip — hiring your spouse can save taxes on medical costs, pension contributions and child care credits. Tax breaks may differ depending on the type of business entity.

Should I file Amended Tax Return? When?

You must file an amended:

There is an error on your filing status (singles filling as married), number of dependent or other facts that make your deduction or exemption higher than what should it have been. These errors result in additional tax if IRS finds the errors before you make any amendment, you may owe interest and penalties. If the error is presumed to be intentional you may be facing audit. All this could be avoided by filing an amended return.

There is omission of income on your return: if you did not include a certain income in your return, amending your return sooner will save you interest and penalty if the omission is significant. But if the omitted income is not significant you may not have to amend your return, in this case you may want until the IRS sends you a bill for the understatement plus interest.

Filing an amended return can benefit you:

If you did not claim certain deduction or credit that may result in tax refunds or if the tax law changed towards your benefit.

Be sure to file for the refund within the time limits set by law. This is usually 3 years from the due date of the return to which the refund relates.

You may not need to file an amended return:

You made calculation error when you file, this will simply be corrected by the computer and you may get a bill or a refund depending on the error. Similarly if you failed to attach certain documents you do not need to amend your return, if IRS needs those documents it will send you a letter requesting you to furnish them.

Need more time to file tax?

Some tax deadlines are as they say “Carved on stone” but others could be changed if took the necessary steps needed. If you need time to file your income tax return all you have to do is submit an extension request form 4868 on or before the filing date deadline (which usually is April 15th every year), note that you do not have to give reason for needing the extension or even have to sign this the form. But remember you have to estimate the tax you owe the best you can and pay your estimated tax, it always is a good idea to pay as much tax as you estimate to minimize and avoid any late interest and penality.

Please note that extending the date of file only gets you time to file not time to pay, thus any balance unpaid is subject additional interest payment.

Business Tax Tip for Workers on Temporary Assignment.The Travel Expenses Can be Deductible

As long as the temporary assignment to a different work location is expected to last and does last one year or less, the travel expenses are tax deductible.

If You Closed Your Business Last Year or This Year Expenses You Continue to Pay May Still be Deductible

If some expenses from a closed business have continued, such as a loan you personally guaranteed, that expense is still deductible, even though the closed business is no longer generating income.

Contributing Property to Your Business; There are Rules on Tax Treatment of the Exchange

The tax treatment of property contributions can vary depending on the type of business entity.

Employer Identification Number (EIN) When Does Your Business Need One?

Sole proprietors generally do not need an EIN unless they hire employees, but other business entities (corporation, partnership and LLC) generally will need to obtain one.

Meal Rates for Day Care Providers Makes Keeping Track of Meal Expenses Easy

The IRS’sstandard rates for meal expense deductions for day care providers greatly simplifies the task of tracking the amounts for tax deductions.

Debit cards are permitted for health reimbursement arrangements and flexible spending accounts.

Deduct Tuition Payments to a Religious School? The IRS says, “No!”

In a private letter ruling, the IRS determined that payment of parochial school tuition is not deductible as a charitable gift, because the parents receive a benefit for the payment in the form of the educationfor their child. The IRS has previously held that “donations” to a religious organization that operates a school with the understanding that the donor’s child will attend the school at no additional cost likewise is not a charitable deduction.

My Stock Tanked – Can I Write-Off the Loss?

A loss on a capital asset can offset a taxable capital gain, and can be used to offset up to $3,000 of other income each year. If your loss exceeds $3,000 in any year, you are allowed to carry it forward to future years and use $3,000 each year to offset other income until the full amount of your loss is used up.If you use married filing separate filing status, however, the annual net capital loss deduction limit is only $1,500.

We communicate with our clients primarily via mail, e-mail, phone, SMS, and fax. Most of our clients require Maryland, DC and Virginia income tax returns as well as federal tax returns, however, we prepare any state income tax return a client requires.

ለንግድ ስራ ገቢ ግብር ማጠቀሻዎች

ለግል መኪና(አዉቶሞቢል)፣ ጭነት ማመላሻ (ትራክ) እና የመንገደኛ ማመላለሻ መኪና (ቫን)እንዲሁም ኤስዩቪ እና ፒክአፕ መኪኖች ለመጀመሪያ ጊዜ በግብር ዓ.ም. 2014 በስራ ላይ ከዋለ ተቀናናሽ የሚደረገዉ የእርጅና መጠን ከፍጠኛ ጣሪያ ከዚህ እንደሚከተለዉ ይሆናል

አነስተኛ የግል መኪና

  • $3,160 ለመጀመሪያዉ የግብር አመት;
  • $5,100 ለሁለተኛዉ የግብር አመት;
  • $3,050 ለሶስተኛዉ የግብር አመት እና
  • $1,875 አራተኛዉ እና ከዚያ ቀጥሎ የሚገኙ ተከታተይ የግብር አመታት።

ጭነት ማመላሻ (ትራክ) እና የመንገደኛ ማመላለሻ ሚኪና (ቫን)

  • $$3,460 ለመጀመሪያዉ የግብር አመት;
  • $5,500 ለሁለተኛዉ የግብር አመት;
  • $3,550 ለሶስተኛዉ የግብር አመት እና
  • $1,975 አራተኛዉ እና ከዚያ ቀጥሎ የሚገኙ ተከታተይ የግብር አመታት።

ኤስዩቪ እና ፒክአፕ መኪኖች $25,000.00 በአመት ነዉ ነዉ።

የማይሌጅ አበል በማይል ለ2014 የግብር ዘመን ለንግድ ድርጅቶች 56 ሳንቲም በማይል ሲሆን ለህክምና እና እቃ ማመላለሻ አገልግሎት መኪኖች ደግሞ 23.5 ሳንቲም በማይል ነዉ። ከዚህ በተጨማሪ ለንግድ ስራ አገልግሎት ለዋሉ መኪኖች ግብር ከፋዩ በአንድ ጊዜ ከአምስት መኪኖች በላይ የማይል ተቀናናሽ ሊጠይቅበት አይችልም። እነዚህ አበሎች መኪኖች ለመነዳት የወጣላቸዉን ወጪ ሰነዶችን መያዝ ሳያስፈልግ በቀላሉ ለማወራረድ ይረዳሉ። ነገር ግን የማይሌጅ መዝገብ መያዝ እጅግ አስፈላጊ ነዉ።፡በዚህ መዝገብ ላይ ጉዞዉ የተከናወነበትን ቀን፣ ጉዞዉ የተካሄደበትን ምክንያት፣ መዳረሻ እንዲሁም የመኪናዉ ኦዲዮሚትር የሚያሳየዉን ቁጥር አንብቦ በትክክል እና በጥንቃቄ መመዝገብ አለበት።

ባለቤቶን የድርጅቶ ሰራተኛ አድርገዉ ሲቀጥሩ በህክምና ወጪ፣ በጡረታ መዋጮን እንዲሁም በልጅ እንክብካቤ ተቀናሽ ግብር ሊያድኑ ይችላሉ። በዚህ ሁኔታ የሚሰጠዉ የግብር እፎይታ እንደ ድርጅቶ አወቃቀር ይለያያል።

የተስተካከለ የግብር ማስታወቂያ ማስገባት ይኖርብኝ ይሆን? መቼ?

የተስተካከለ የግብር ማስታወቂያ የግዴታ ማስገባት የሚኖርቦ፡

የግብር ማስታወቂያዎን ሲያሰሩ የተሳሳተ የግብር ከፋይ ምድብ ዉስጥ ገብተዉ ከነበር (እንደ ግለሰብ ግብሮን ማስታወቅ ሲገባዎ እንደ ተጋቢ ጥንድ የጋራ የግብር ማስታወቂያ ካሰሩ)፣ የጥገኞች ተቀናናሽ በህጉ መጠየቅ ከሚገባዎ ከፍ ብሎ ከሆነ። እነዚህ ስህተቶች ተጨማሪ ግብር እና ቅጣት ከነወለዱ ሊያስከትሉ ይችላሉ። ስለሆነም አይአርኤስ ስህተቶቹን ሳይደርስባቸዉ እርሶ ማስተካከያ ካስገቡ የሚከፍሉትን ቅጣት እና ወለድ ሊቀንሱ ይችላሉ። ነገር ግን ይህ ስህተት ከተደረሰበት በተለይም ደግሞ ግብር ከፋዩ አዉቆ ያደረገዉ ነዉ የሚል ግምት ከተወሰደ ኦዲትም ሊያስከትል ይችላል።

ግብር የሚከፈልበትን ገቢዎን ሲያስታዉቁ የተወሰኑ ገቢዎች ሳይካተቱ ተዘለዉ የቀሩ ከሆነ እና የተዘለለዉ የገቢ መጠንም በመጠኑ ከፍተኛ ከሆነ እነዚህን ገቢዎች ያካተተ የተስተካከለ የግብር ማስታወቂያ በተቻለ ፍጥነት ማስገባት ይኖርቦታል። ይህንን በማድረጎ ወለድ እና ቅጣት ያድንሎታል። ነገር ግን ይህ የተዘለለዉ መጠን ከፍተኛ ካልሆነ የገቢ ግብር ማስተካከያ ማስታወቂያ ማሰራት ላያስፈልጎ ይችላል። ይህ ከሆነ አይአርኤስ ስህተቱን ደርሶበት ለእርሶ የክፍያ ማስታወቂያ እስኪልክሎ ይጠብቁ። የሚላክሎ ቢል ሳይከፈል በልዩነት የቀረዉን ግብር እና ወለድ ይጨምራል።፡

የተስተካከለ የግብር ማስታወቂያ ማስገባት እርሶን ይጠቅም ይሆናል፡

አንድአንድ ተቀናሾች እና የግብር ተመላሾች በግብር ማስታወቂያዎ ላይ ሳያካትቱ ቀርተዉ ከነበረ እና እነዚህም ሲስተካከሉ ለእርሶ የግብር ተመላሽ ሊያስገኝሎ ከቻሉ ወይንም ደግሞ የግብር ህጉ እርሶን በሚጠቅም መልኩ ከተለወጠ የተስተካከለ የግብር ማስታወቂያ ማስገባቶ ጥቅም ሊያስገኝሎ ይችላል።

የግብር ማስተካከያ ተመላሾን በህግ በተሰጠዉ የጊዜ ገደብ ዉስጥ ማስታወቆን ብቻ እርግጠኛ ይሁኑ። ይህ የጊዜ ገደብ አብዛኛዉን ጊዜ ተመላሹ ግብር ከሚመለከተዉ የግብር ማስታወቂያ የመጨረሻ ቀን አንስቶ እስከ ሶስት አመታት ይዘልቃል።

ምንም አይነት ማስተካከያ ላየስፈልጎ ይችላል፡

የግብር ማስታወቂያዎ ሲሰራ የሂሳብ ስህተት ከነበረዉ ይህ በቀላሉ በኮንፒዉተሩ ተሰልቶ ስለሚስተካከል እና ለልዩነቱም ተገቢዉ የክፍያ መጠየቂያ ቢል ወይንም የግብር ተመላሽ ስለሚላክሎ እርሶ ምንም አይነት ማስተካከያ ማድረግ አያስፈልጎትም። በተመሳሳይም ሰነዶች ከግብር ማስታወቂያዉ ጋር ሳያያይዙ ከቀሩ ምንም ተጨመሪ ማስተካከያ ማስገባት አያስፈልጎትም። አይእርኤስ ሰነዶቹ ካፈለገ በደብዳቤ እንዲያቀርቡ ይጠይቆታል።

ግብርኦን ለማስታወቅ ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልጎታል?

አንዳንድ የግብር ማስታወቂያ የጊዜ ገደቦች በድንጋይ የተፃፉ ይመስል ቀናቸዉን መለወጥ አዳጋች ነዉ። ነገር ግን ሌሎች ደግሞ አስፈላጊዉን ቅድመ ሁኔታ በሟሟላት በቀላሉ ሊቀየሩ ይችላሉ። የገቢ ግብሮን ለማስታወቅ ተጨማሪ ጊዜ ካስፈለጎ ማድረግ የሚጠበቅቦ የግብር ዘመኑ የማስታወቂያ የጊዜ ገደብ ሳያልፍ ቅፅ ቁጥር 4868 ሞልተዉ ማስገባት ብቻ ነዉ (አብዛኛዉን ጊዜ ኤፕሪል 15 ሳያልፍ)። ያስተዉሉ ለምን ጊዜዉን ማራዘም እንዳስፈለጎ እንዲያስረዱም ሆነ ምክንያት እንዲያቀርቡ አይጠየቁም። እንዳዉም ፎርሙን ሁሉ መፈረም አይገደዱም። ነገር ግን ማስተዋል እና ማስታወስ ያለቦ ቁምነገር ግብሮን በተቻለ መጠን የተስተካከለ ግምት በመያዝ መክፈሎ እንዳለቦ ነዉ። ካልተከፈለ ግብር ጋር ተያይዞ የሚመጣዉን ቅጣት ለመቀነስ ሁል ጊዜ ተመራጭ የሚሆነዉ መክፈል የሚችሉትን ግምታዊ ግብር በሙሉ መክፈል ነዉ።

ያስተዉሉ የጊዜ ገደቡን ማራዘም የገቢ ግብር ማስታወቂያ የሚያስገቡበትን ቀን ያራዝምሎታል እንጂ ተጨማሪ የክፍያ የጊዜ ገደብ አይሰጦትም ስለሆነም ሳይከፍሉ በቀሩት መጠን ላይ ወለድ ይጠየቃሉ።

የንግድ ስራ ግብር ማጣቀሻ በስራ በጊዚያዊነት ተመድበዉ ላኘሉ ሰራኞች፡ የመጓጓዣ እና መመለላለሻ ወጪዎ ለቀናነስ ይችላል!!

ለስራ በጊዚያዊነት ተዛዉረዉ በመደበኛነት ከሚሰሩበት የስራ ቦታዎ ከተንቀሳቀሱ እና ይህዉ ጊዛዊ ምድብ ከአንድ አመት እና ከዚያ በታች ብቻ ቆይታ ካለዉ የመመላለሻ እና መጓጓዣ ወጪዎ ለግብር ተቀናናሽ ይደረጋል።

የንግድ ስራዎን የዘጉት ባለፈዉ የግብር አመት ወይንም በዚህ የግብር ዘመን ሆኖ እስከ አሁን ወጮዎች እየከፈሉ ካሉ ይህም ተቀናናሽ ሊሆን ይችላል።

አንዳንድ ወጪዎችን ባለፈዉ ወይንም በዚህኛዉ አመት ለዘጉት የንግድ ድርጅት እየከፈሉ ከሆነ፣ ለምሳሌ በእርሶ የግል ዋስትና ላገኙት ብድር የሚከፍሉት ወጪ፣ የዘጉት ድርጅት ምንም ገቢ እያስገኘሎት ባይሆንም እንዃ ይህ ወጪ ግብር ከሚከፍሉበት ገቢ ላይ ተቀናናሽ የደረጋል።

ለድርጅቶ የሚያዋጡት የአይነት- የንብረት መዋጮን በተመለከተ የአይነት በአይነት ልዉዉጥን (ከጥሬ ገንዘብ ዉጪ ያለ ንብረትን መወጮን በባለቤትነት መብት መለወጥ) አስመልክቶ የግብር ህጉ የተለየ ስርዓት አለዉ

ይህ ከጥሬ ገንዘብ ዉጪ ያለ የንብረት መዋጮ እንደ ድርጅቶ አወቃቀር አይነት ይለያያል።

የቀጣሪዎች የግብር መለያ ቁጥር (ኢአይኤን)፡ ድርጅቶ ይህ የመለያ ቁጥር መቼ ያስፈልገዋል?

በግል ባለቤትነት የሚያስተዳድሩት ድርጅት ከሆን ኢአይኤን መለያ ቁጥር ሰራተኞች እስካልቀጠሩ ድረስ አያስፈልጎትም። ነገር ግን ሌሎች ድርጅቶች (ኮርፕሬሽኖች፣ ሽርክናዎች እና ሃላፊነታቸዉ የተወሰነ ኩባንያዎች) በሙሉ ይህ የመለያ ቁጥር ያስፈልጋቸዋል።

የእንክብካቤ አገልግሎት ለሚሰጡ ተቌሞች የሚሰጠዉ የምግብ አቅርቦት አበል እነዚህ ድርጅቶች የመብል አቅርቦት ወጪያቸዉን ቀልል ባለ መለኩ ለማወራረድ ያስችላቸዋል

አይአርኤስ የእንክብካቤ አገልግሎት ለሚሰጡ ተቌሞች ለመብል አገልግሎት አቅርቦት የሚሰጠዉ መደበኛ ተቀናናሽ የአበል ምጣኔ ግብር ከሚከፈልበት ገቢ ላይ ለዚህ አገልግሎት የዋለዉን ወጪ በቀላሉ ለማስላት ያስችላል።

የዴቢት ካርድ በጤና ወጪ ተመላሽ ስምምነት እና በተዋዋጭ ክፍያ ሂሳብ ስምምነት መሰረት ለተከፈለ የህክምና ወጪን ለማወራረድ ይፈቀዳል።

ለሃይማኖት ተቌማት የሚከፈል የትምህርት ክፍያ ማቀናነስ ይፈልጋሉ? አይአርኤስ አይቀነስም ይላል!

ለአንድ ግብር ከፋይ በተጳፈ የደብዳቤ ማስታወቂያ ላይ አይአርኤስ ለተለዩ እምነት ተቌማት የትምህርተ አገልግሎት የተከፈለ ክፍያ እንደ በጎ አድራጎት ስጦታ ግብር ከሚከፈልበት ገቢ ላይ ተቀናሽ መደረግ እንደማይችል አቌሙን ገልፆል። ምክንያቱም ወላጆች ለሰጡት ስጦታ ልጆቻቸዉ በማስተማር ተለዋጭ ጥቅም ስለሚያገኙ ነዉ። ከዚሁ ጋር በተያያዘ አይ አር ኤስ ወላጆች የትምህርት መርሃ ግብር ላላቸዉ እምነት ተቌማት በሚያዋጡት መወጮ ብቻ ልጆቻቸዉ ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ በእምነት ተቌሙ ትምህርት ቤት ዉስት ማስተማር የሚችሉ ከሆነ በእንዲህ አይነት ሁኔታ የሚዋጣ መዋጮ ግብር ከሚከፈልበት ገቢ ላይ ተቀናሽ እንደማይደረግ አስታዉቌል።

በመጋዘን የተከማቸዉ የንግድ እቃዬ ዋጋ አሽቆለቆለ- የደረሰብኝን ኪሳራ ማወራረድ እችላለሁ?

በሃብትነት በተያዙ ንብረቶች የደረሰቦትን ኪሳራ አንዲሁ ከተያዙ ንብረቶች ላይ ካገኙት ትርፍ ላይ ማቀናነስ ይችላሉ ነገር ግን የደረሰቦ ኪሳራበሃብትነት ከያዙት ንብረት ካገኙት ትርፍ ተቀናንሶ ኪሳራዉ በሙሉ መወራድ ካልቻለ ከሌላ ምንጭ ካገኙት ገቢ ላይ በየአመቱ እስክ $3,000 ድረስ የደረሰቦት የኪሳራ መጠን ተቀናንሶ እስከሚያበቃ ማቀናነስ ይችላሉ። ይህ መጠን ባለትዳሮች ለየብቻ የግብር ማስታወቂያቸዉን ሲያሰሩ $1,500 ይሆናል።

ከደንበኞቻችን ጋር በዋንኛነት በኢሜል፣ በስልክ፣ በአስኤምኤስ እና ፋክስ እንገናኛለን። አብዛኛዉ ደንበኞቻችን የሜሪላንድ፣ ዲሲ እና ቨርጂኒያ ስቴት እና ፌደራል የገቢ ግብር ማስታወቂያ ይፈልጋሉ ነገር ግን ደንበኞቻችን ለሚፈልጉት ማንኛዉም ስቴት የገቢ ግብር ማስታወቂያ እናዘጋጃለን።